በጌምድር አካዳሚ


Kanal geosi va tili: O‘zbekiston, Forscha



Kanal geosi va tili
O‘zbekiston, Forscha
Statistika
Postlar filtri




የተከበራችሁ የበጌምድር አካዳሚ የተማሪ ወላጆችና አሳዳጊዎች፦

​ቀደም ሲል ከአካዳሚያችን አጥር ተጠግቶ ሊካሄድ ታስቦ የነበረውን የጤና ተቋም ግንባታ በተመለከተ፣ በፍርድ ቤት ሂደቱ እና በአመራሩ በኩል የተደረሱ ስምምነቶችን መነሻ በማድረግ መረጃ አቅርበንላችሁ እንደነበር ይታወቃል።

​ሁለቱም ወገኖች በተደረሰው ስምምነት መሰረት በፍርድ ቤት ቀርበው በመፈራረም ውሳኔውን ለማፅናት የተዘጋጁ ቢሆንም፤ የPSSEJ ሙሉ ውክልና ያለው ተወካይ በፍርድ ቤት ቀርቦ ለመፈረም ባለመፈለጉ ምክንያት የተደረገው ስምምነት ሳይጸና ቀርቷል።

​በዚህም ምክንያት ክርክሩ የቀጠለ ሲሆን፣ በፍርድ ቤቱ በኩል የነበረው የግንባታ እግድ እንዲነሳ ውሳኔ ተሰጥቷል። ነገር ግን የአካዳሚያችን አመራሮች እና የወላጅ ኮሚቴ የልጆቻችንን ጤና፣ ደህንነት እና የትምህርት ቤቱን ህልውና አሳልፎ ላለመስጠት ባላቸው ጽኑ አቋም፦

✅ ​ይግባኝ በመጠየቅ እስከ ሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ ህጋዊ ሙግታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፤

✅ ​የልጆቻችንን ሰላምና ደህንነት የሚያስጠብቁ ሁሉንም ህጋዊ አማራጮች ለመጠቀም ዝግጅታችንን ማጠናቀቃችንን እንገልፃለን።

​ጉዳዩ በአሁኑ ወቅት በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የአካዳሚያችን አመራር እና የወላጅ ኮሚቴ ሂደቱን በጥብቅ እየተከታተሉ የደረሰበትን ደረጃ ወደፊትም ለእናንተ ለተከበራችሁ ወላጆች እና አሳዳጊዎች የምናሳውቅ ይሆናል።

​ለምናደርገው ጥረት ከጎናችን በመሆን ለምታሳዩት ትብብር እና ድጋፍ ከልብ እያመሰገንን፣ ምንም አይነት ስጋት ሳይገባችሁ ከመደበኛው የመማር ማስተማር ጎን እንድትቆሙ እናሳስባለን።

​ከሰላምታ ጋር፣

በጌምድር አካዳሚ


የ2019 ዓ.ም የቅድመ አንደኛ ተማሪዎች የትምህርት መጀመሪያ ቀን

https://vt.tiktok.com/ZSbA1Wjfv/




ፋይናንስ ክፍል በጌምድር አካዳሚ dan repost
ከክፍያ ጋር የተያያዙ መመሪያዎችን የአከፋፈል ሂደቶችን የክፍያ ጊዜ ከቅጣት በፊት
ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይንኩና ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/FinanceBegaimeder

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️


ማስታወቂያ

​ጉዳዩ፦ ትምህርት ቤት የመግቢያ ሰዓትን ይመለከታል

​የአካዳሚው ሰርቪስ (የትምህርት ቤት ባስ) ሳትጠቀሙ በግል ትራንስፖርት (በሚኒቫስ፣ በባጃጅ) እንዲሁም በእግር የምትመጡ ተማሪዎች፤ የትምህርት ቤት የመግቢያ ሰዓት የመጨረሻ 2:00 መሆኑን ያሳውቃል።
​ተማሪዎች የትምህርት ሰዓታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ እና የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዳይስተጓጎል እስከ 2:00 ሰዓት ድረስ ትምህርት ቤት ተገኝተው እንዲገቡ ወላጆች አስፈላጊውን ክትትል እና ትብብር እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።

​ከሰላምታ ጋር!

አካዳሚው


​🔔 አስፈላጊ ማስታወቂያ ለቅድመ መደበኛ ወላጆች/አዳጊዎች

​የተወደዳችሁ ወላጆች፤
​ከዚህ ቀደም የቅድመ መደበኛ ትምህርት የሚጀመርበትን ቀን ወደፊት እንደምናሳውቅ መግለጻችን ይታወቃል።

​በመሆኑም መምህራኖች ከሰለጠኑበት ኮሌጅ ሰኞ ወደ ትምህርት ቤት የሚመለሱ በመሆኑ፣ በዕለቱ የልጆችን መማሪያ ክፍሎች በማዘጋጀት እና ለህፃናት በሚሆን መልኩ ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ ይረባረባሉ።
​ስለሆነም፡
📅 ትምህርት የሚጀመርበት ቀን፡ ማክሰኞ መስከርም 19/2019 ዓ.ም በመሆኑ

​ውድ ወላጆች ልጆቻችሁ በተገለፀው ቀን ለትምህርት አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶቻቸውን አሟልተው ለትምህርት ዝግጁ ሆነው እንዲመጡ በአክብሮት እናሳስባለን።

​ከሰላምታ ጋር፤


መማሪያ መጽሐፍ ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉትን የምትማሩበትን ክፍል በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ

🔹 1ኛ ክፍል

🔹 2ኛ ክፍል

🔹 3ኛ ክፍል

🔹 4ኛ ክፍል

🔹 5ኛ ክፍል

🔹 6ኛ ክፍል

🔹 7ኛ ክፍል

🔹 8ኛ ክፍል

ማሳሰቢያ ለኛ የክፍል ደረጃ በComments በሚለው አትላኩ ለምሳሌ ልጅው አንደኛ ክፍል ከሆነ 1ኛ ክፍል የሚለውን ከዝርዝሩ ይጫኑ
አካዳሚው


ከትምህርት ቤት ወደ ቤት የሚመለሱበት የትራንስፓርት ፕሮግራም


ከቤት ወደ ትምህርት ቤት የሚመጡበት የትራንስፓርት ፕሮግራም


👍


ሰላማዊ የመማር መሰተማር ሂደትን በማሰፈን የትምህርት ጥራትን በማሰጠበቅ፣ የደንበኞችን ፍላጎት 100% ለማርካት ቆርጦ የተነሳ የመማር ማሰተማር ቁርጠኛ አቋም በርታ ከጎንህ አለን።


📢 እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!

ውድ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች እና ወላጆች/አዳጊዎች፤
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መጀመሩን አስመልክቶ ትምህርታችን ስኬታማ፣ የተቀናጀና ውጤታማ ይሆን ዘንድ ከእያንዳንዱ ተማሪ እና ወላጅ የሚጠበቁ ዋና ዋና ኃላፊነቶች እንደሚከተለው የቀረቡ በመሆኑ ሁሉም አካል አስፈላጊውን ዝግጅትና ክትትል እንዲያደርግ በአክብሮት እንጠይቃለን።

⚠️ በጣም አስፈላጊ ማሳሰቢያዎች፡
የትምህርት ሰዓትን በተመለከተ፡

ከሰኞ መስከረም 11 ጀምሮ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ትምህርት ሙሉ ቀን የሚሰጥ ይሆናል።
ተማሪዎች ሙሉ ቀን ለመማር አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገው እንዲመጡ፤ ወላጆችም ይህንን ተረድተው አስፈላጊውን ቁሳቁስና ምግብ/ምሳ አሟልተው እንዲልኳቸው እናሳስባለን።
የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) በተመለከተ፡
የትምህርት ቤቱን ዩኒፎርም ያላሟሉ ተማሪዎች ወደ ክፍል ውስጥ የማይገቡ መሆኑን አጥብቀን እናሳውቃለን።
ዩኒፎርም ያላሟላችሁ ወላጆች በእለቱ ትምህርት ቤት በመምጣት ዩኒፎርም በመግዛት ለልጆቻችሁ እንድታለብሱ እናሳስባለን።
የደብተር መረጃ እና የግብ ፎርማት፡
ሁሉም ተማሪዎች በየደብተራቸው የመጀመሪያ ገጽ ላይ ከዚህ በታች ያለውን ፎርማት ጽፈው/ሞልተው እንዲመጡ ወላጆች ክትትል እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡
ሙሉ ስም: ___________________________
ክፍል/ሴክሽን: ___________________
የትምህርት ቤት: _________________________
የትምህርት ዘመን: ___________________
የትምህርት አይነት: ___________________
በዚህ የትምህርት አይነት ለማስመዝገብ ያቀድኩት ውጤት [_________%] ነው!
📌 1. ከተማሪዎች የሚጠበቁ ኃላፊነቶች
ትጋትና ዝግጁነት፡

ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ግልጽ ግብ ማስቀመጥ እና አዎንታዊ አስተሳሰብ መያዝ።
ሰዓትና ደንብ ማክበር፡ በሰዓቱ መገኘት፣ የትምህርት ቤቱን ውስጠ-ደንብና የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) በአግባቡ ማክበር።
የጥናት ልማድና የቤት ስራ፡ የዕለት ተዕለት የጥናት ፕሮግራም ማውጣት፣ የሚሰጡ የቤት ስራዎችንና ፕሮጀክቶችን በጊዜው ሰርቶ ማጠናቀቅ።
ንቁ ተሳትፎ፡ በክፍል ውስጥ በሚደረጉ ውይይቶችና ጥያቄና መልሶች ላይ በንቃት መሳተፍ።
ቁሳቁስን መንከባከብ፡ የመጽሐፍትና ደብተሮች ንጽህና መጠበቅ።

👨‍👩‍👧‍👦 2. ከወላጆች የሚጠበቁ ኃላፊነቶች
ቁሳቁስና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ፡ ደብተር፣ መጽሐፍትና ዩኒፎርም በጊዜው ማሟላት፤ ለልጅዎ ምቹ የጥናት ቦታ በመመደብ ስነ-ልቦናዊ ማበረታቻ መስጠት።
የዕለት ተዕለት ክትትል፡ የልጅዎን ደብተር፣ የቤት ስራ እና የክፍል ስራዎች በየቀኑ ማየትና በCommunication Book መፈረም።
የጊዜ አጠቃቀምን መቆጣጠር፡ ልጅዎ በሰዓቱ እንዲተኛና እንዲነቃ ማድረግ፤ የማህበራዊ ሚዲያና የስልክ አጠቃቀም ጊዜን መገደብ።
ከትምህርት ቤት ጋር ትብብር ማድረግ፡ በመደበኛ የወላጅ-መምህር ስብሰባዎች ላይ መሳተፍ፣ ከመምህራን ጋር ስለ ልጅዎ ባህሪና ውጤት በቅርብ መነጋገር።

✨ በጋራ በመስራት ለልጆቻችን ብሩህ ተስፋና ስኬት እንትጋ!

መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንልን!


የ2019 ዓ.ም ወርሃዊ የተማሪዎች የትምህርት ክፍያ የጊዜ ሴለዳ እና ተያያዥ ጉዳዮች በፋይናስ ቴሌግራም ገጽ ስለተለቀቀ ከዚህ ስር የተቀመጠውን በመንካት ገብተው ይመልከቱ ከፋይናስ ጋር የተያያዙ መረጃዎች ከዚህ በታች ባለው ቻናል ብቻ ስለሚለቀቅ ተከታተሉ
👇👇👇👇👇👇

👉 የፋይናንስ ቻናል

☝️☝️☝️☝️☝️☝️


የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች የሴክሽን ድልድል ከ1ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል እየተለቀቀ ስለሆነ ለማግኘት የልጅዎን የክፍል ደረጃ በመጫን በመግባት መማሪያ ሴክሽናቸውን መመልከት ይቻላል

🔹 1ኛ ክፍል

🔹 2ኛ ክፍል

🔹 3ኛ ክፍል

🔹 4ኛ ክፍል

🔹 5ኛ ክፍል

🔹 6ኛ ክፍል

🔹 7ኛ ክፍል

🔹 8ኛ ክፍል

📍 መስከረም 06 / 2018 ዓ.ም

አካዳሚው

3.7k 0 0 15 116

​🚨 ጥብቅ መልዕክት ለበጌምድር አካዳሚ የተማሪ ወላጆች / አሳዳጊዎች 🚨

​ቀን፡ 06/01/2019 ዓ.ም

👉 ​ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት፡
የ2019 ዓ.ም የመደበኛ ትምህርት መማር ማስተማር ስራ ግቢው ውሃ የመቋጠር ችግር ስለነበረበት መስከረም 11 ቀን ይጀመራል ተብሎ የተገለፀ ቢሆንም፤ በተደረገው ከፍተኛ እርብርብ የግቢው ውሃ የተቋጠረበት ቦታ በአፈር በመሞላቱና የዝናብ እጥረት በመከሰቱ ግቢው ጠፈፍ ብሏል።

​ስለሆነም ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያላችሁ መደበኛ ተማሪዎች በነገው ዕለት ሐሙስ (ቀን 07/01/2019 ዓ.ም) ትምህርት የሚጀመር መሆኑን አውቃችሁ በተለመደው የትራንስፖርት/ፊርማታ ቦታ እንድትጠብቁ ትምህርት ቤቱ ያሳስባል።

👉 ​የቅድመ መደበኛ (KG) ህፃናት ትምህርት፡
የቅድመ መደበኛ ህፃናት ትምህርት የሚጀምርበትን ቀን የመምህራኖቻቸው የኮሌጅ ስልጠና እንደተጠናቀቀ አያይዘን የምናሳውቅ ይሆናል።

​በጌምድር አካዳሚ
"ትምህርት በጥራት እንሰጣለን!"









20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.