የተከበራችሁ የበጌምድር አካዳሚ የተማሪ ወላጆችና አሳዳጊዎች፦
ቀደም ሲል ከአካዳሚያችን አጥር ተጠግቶ ሊካሄድ ታስቦ የነበረውን የጤና ተቋም ግንባታ በተመለከተ፣ በፍርድ ቤት ሂደቱ እና በአመራሩ በኩል የተደረሱ ስምምነቶችን መነሻ በማድረግ መረጃ አቅርበንላችሁ እንደነበር ይታወቃል።
ሁለቱም ወገኖች በተደረሰው ስምምነት መሰረት በፍርድ ቤት ቀርበው በመፈራረም ውሳኔውን ለማፅናት የተዘጋጁ ቢሆንም፤ የPSSEJ ሙሉ ውክልና ያለው ተወካይ በፍርድ ቤት ቀርቦ ለመፈረም ባለመፈለጉ ምክንያት የተደረገው ስምምነት ሳይጸና ቀርቷል።
በዚህም ምክንያት ክርክሩ የቀጠለ ሲሆን፣ በፍርድ ቤቱ በኩል የነበረው የግንባታ እግድ እንዲነሳ ውሳኔ ተሰጥቷል። ነገር ግን የአካዳሚያችን አመራሮች እና የወላጅ ኮሚቴ የልጆቻችንን ጤና፣ ደህንነት እና የትምህርት ቤቱን ህልውና አሳልፎ ላለመስጠት ባላቸው ጽኑ አቋም፦
✅ ይግባኝ በመጠየቅ እስከ ሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ ህጋዊ ሙግታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፤
✅ የልጆቻችንን ሰላምና ደህንነት የሚያስጠብቁ ሁሉንም ህጋዊ አማራጮች ለመጠቀም ዝግጅታችንን ማጠናቀቃችንን እንገልፃለን።
ጉዳዩ በአሁኑ ወቅት በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የአካዳሚያችን አመራር እና የወላጅ ኮሚቴ ሂደቱን በጥብቅ እየተከታተሉ የደረሰበትን ደረጃ ወደፊትም ለእናንተ ለተከበራችሁ ወላጆች እና አሳዳጊዎች የምናሳውቅ ይሆናል።
ለምናደርገው ጥረት ከጎናችን በመሆን ለምታሳዩት ትብብር እና ድጋፍ ከልብ እያመሰገንን፣ ምንም አይነት ስጋት ሳይገባችሁ ከመደበኛው የመማር ማስተማር ጎን እንድትቆሙ እናሳስባለን።
ከሰላምታ ጋር፣
በጌምድር አካዳሚ