📢 እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!
ውድ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች እና ወላጆች/አዳጊዎች፤
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መጀመሩን አስመልክቶ ትምህርታችን ስኬታማ፣ የተቀናጀና ውጤታማ ይሆን ዘንድ ከእያንዳንዱ ተማሪ እና ወላጅ የሚጠበቁ ዋና ዋና ኃላፊነቶች እንደሚከተለው የቀረቡ በመሆኑ ሁሉም አካል አስፈላጊውን ዝግጅትና ክትትል እንዲያደርግ በአክብሮት እንጠይቃለን።
⚠️ በጣም አስፈላጊ ማሳሰቢያዎች፡
የትምህርት ሰዓትን በተመለከተ፡
ከሰኞ መስከረም 11 ጀምሮ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ትምህርት ሙሉ ቀን የሚሰጥ ይሆናል።
ተማሪዎች ሙሉ ቀን ለመማር አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገው እንዲመጡ፤ ወላጆችም ይህንን ተረድተው አስፈላጊውን ቁሳቁስና ምግብ/ምሳ አሟልተው እንዲልኳቸው እናሳስባለን።
የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) በተመለከተ፡
የትምህርት ቤቱን ዩኒፎርም ያላሟሉ ተማሪዎች ወደ ክፍል ውስጥ የማይገቡ መሆኑን አጥብቀን እናሳውቃለን።
ዩኒፎርም ያላሟላችሁ ወላጆች በእለቱ ትምህርት ቤት በመምጣት ዩኒፎርም በመግዛት ለልጆቻችሁ እንድታለብሱ እናሳስባለን።
የደብተር መረጃ እና የግብ ፎርማት፡
ሁሉም ተማሪዎች በየደብተራቸው የመጀመሪያ ገጽ ላይ ከዚህ በታች ያለውን ፎርማት ጽፈው/ሞልተው እንዲመጡ ወላጆች ክትትል እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡
ሙሉ ስም: ___________________________
ክፍል/ሴክሽን: ___________________
የትምህርት ቤት: _________________________
የትምህርት ዘመን: ___________________
የትምህርት አይነት: ___________________
በዚህ የትምህርት አይነት ለማስመዝገብ ያቀድኩት ውጤት [_________%] ነው!
📌 1. ከተማሪዎች የሚጠበቁ ኃላፊነቶች
ትጋትና ዝግጁነት፡
ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ግልጽ ግብ ማስቀመጥ እና አዎንታዊ አስተሳሰብ መያዝ።
ሰዓትና ደንብ ማክበር፡ በሰዓቱ መገኘት፣ የትምህርት ቤቱን ውስጠ-ደንብና የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) በአግባቡ ማክበር።
የጥናት ልማድና የቤት ስራ፡ የዕለት ተዕለት የጥናት ፕሮግራም ማውጣት፣ የሚሰጡ የቤት ስራዎችንና ፕሮጀክቶችን በጊዜው ሰርቶ ማጠናቀቅ።
ንቁ ተሳትፎ፡ በክፍል ውስጥ በሚደረጉ ውይይቶችና ጥያቄና መልሶች ላይ በንቃት መሳተፍ።
ቁሳቁስን መንከባከብ፡ የመጽሐፍትና ደብተሮች ንጽህና መጠበቅ።
👨👩👧👦 2. ከወላጆች የሚጠበቁ ኃላፊነቶች
ቁሳቁስና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ፡ ደብተር፣ መጽሐፍትና ዩኒፎርም በጊዜው ማሟላት፤ ለልጅዎ ምቹ የጥናት ቦታ በመመደብ ስነ-ልቦናዊ ማበረታቻ መስጠት።
የዕለት ተዕለት ክትትል፡ የልጅዎን ደብተር፣ የቤት ስራ እና የክፍል ስራዎች በየቀኑ ማየትና በCommunication Book መፈረም።
የጊዜ አጠቃቀምን መቆጣጠር፡ ልጅዎ በሰዓቱ እንዲተኛና እንዲነቃ ማድረግ፤ የማህበራዊ ሚዲያና የስልክ አጠቃቀም ጊዜን መገደብ።
ከትምህርት ቤት ጋር ትብብር ማድረግ፡ በመደበኛ የወላጅ-መምህር ስብሰባዎች ላይ መሳተፍ፣ ከመምህራን ጋር ስለ ልጅዎ ባህሪና ውጤት በቅርብ መነጋገር።
✨ በጋራ በመስራት ለልጆቻችን ብሩህ ተስፋና ስኬት እንትጋ!
መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንልን!