ምንም ብታደርጉ ሰዎች ከማውራት ስለማይመለሱ ዝም
☞ ደሀ ብትሆን የመናጢ ልጅ ፤ ሀብታም ብትሆን ዶላር
ያሳበጠው
ይሉሀል።
☞ ከሴት ጋር ብትሄድ ሴሰኛ ፤ ብቻህን ብትሆን ወፈፌ
ይሉሀል ።
☞ ብትፈጥን ቀዥቃዣ ፥ ብትዘገይ ዘገምተኛ ።
☞ ብታወራ ለፍላፊ ፥ ዝምብትል ዝጋታም ።
☞ ብትራመድ አርፎ አይቀመጥም ፥ አርፈህ ብትቀመጥ ዝፍዝፍ
☞ ብትማር አወቅሁ ባይ ፥ ባትማር የአቡጊዳ ሽፍታ ።
☞ ብትወፍር ጠብደል ፥ ብትከሳ በልቶ ማይጠረቃ ።
☞ ብትይዝ ቋጣሪ ፥ ብትለቅ መንዛሪ ። ...
እንደውም አንድ የሀገራችን ተረት አለ "ባልና ሚስት አህያ
እየነዱ ሲሄዱ ተቺዎች አገኙዋቸውና ፦"እንከፎች አህያዋ ሳለች እንዴት
አይሳፈሩባትም" ሲሉ ባል ሰማና ሚስቱን " በይ ፍጠኚና
አህያዋ ላይ
ተሳፈሪ" - አላት።
ትንሽ እንደሄዱ ሌሎች ተቺዎች ፦ "ይች ባለጌ ፥ ባል
በእግር እየሄደ
ሚስት በጋማ ከብት" ብለው ወረፏቸው።ባል ሚስቱን
አስወርዶ አህያዋ
ወገብ ላይ ቂብ አለ ፤ትንሽ እንደተጋዙ ሌሎች ተቺዎች
አገኝዋቸው ፦
"የተረገመ ሚስቱን በእግር እያስኬደ እሱ በአህያዋ ብለው
ወረዱባቸው
።
ባልና ሚስት ድንገት ቢተዉን ብለው አህያዋ ላይ
ሲፈናጠጡ ሌሎች
ተቺዎች ደም አገኙዋቸውና "ምን እንስሳ ብትሆን ለሁለት
ይከመሩባታል ግፈኞች ..." የስድብ ናዳ ለቀቁባቸው ።
እንግዲህ ወዳጆቼ ፦ አህያዋን ቢሸከሙ ኖሮ ከዚህ
አይብስምን ?
ስለዚህ ሰዎች ያሉትን ይበሉ አንተ አንተነትህን ሁንና
ህሊናህ አውጥቶና
አውርዶ ከተቀበለው ሀሳብ ጋር ተስማማ።
ለጮኸ ውሻ ሁላ ድንጋይ መወርወር ጊዜን ማባከን ነው፡፡
@TRUTHZONE @TRUTHZONE For any comment n suggestion 👉
@Nahizi