💡
ብዙ ማጥናት ማለት ብዙ መማር አይደለም🧠
አንድ ተማሪ በቀን 5 ወይም 6 ሰዓት መጽሐፍ ፊት ለፊት ሊቀመጥ ይችላል : ብዙ ገጾችን ሊያነብ ይችላል : ብዙ ማስታወሻዎችንም ሊጽፍ ይችላል።
ነገር ግን… 🤔
ከእነዚህ ሁሉ በኋላ አንድ ጥያቄ ሲመጣለት “ይህን ጥያቄ ከየት ልጀምረው?” ብሎ ከተደናገረ፣ ችግሩ ያጠናው ሰዓት ብዛት ላይ ብቻ አይደለም።
🈂
የመማር styleህን ተመልከትአንድ ኮርስ ስትማር በቀጥታ ፎርሙላ ወይም የጥያቄ መልስ ለማስታወስ ከሞከርክ፣ በፈተና ጊዜ ትንሽ ለውጥ ያለበት ጥያቄ ሊያደናግርህ ይችላል።
🔘
ለምሳሌ፦🔸
Mechanics Statics ስትማር፣ የEquilibrium ፎርሙላዎችን ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም። ነገሩን ከመጀመሪያ ማየት፣ Free Body Diagram መስራት፣ Forces መለየት፣ Moments መረዳት እና ትክክለኛውን ዘዴ መምረጥ ያስፈልጋል።
🔸
Applied Mathematics ስትማርም ፎርሙላውን ማስታወስ ብቻ አይበቃም። ጥያቄው ምን እንደሚጠይቅ፣ የትኛው ዘዴ እንደሚስማማው እና ያንን ዘዴ በትክክል መተግበር ነው ዋናው።
🎯
ስለዚህ ጎበዝ ተማሪ ማለት…“ብዙ ሰዓት የሚያጠና” ብቻ አይደለም።
ጎበዝ ተማሪ፦
✅ ጽንሰ-ሐሳቡን ይረዳል።
✅ ለምን እንደሚጠቀምበት ያውቃል።
✅ ችግሩን ይተነትናል።
✅ ትክክለኛውን የመፍትሔ ዘዴ ይመርጣል።
✅ በተለያዩ ጥያቄዎች ላይ ይለማመዳል።
✅ ስህተቱን ያያል፣ ይማራል፣ እንደገና ይሞክራል።
መማር ማለት መጽሐፍ ፊት ለፊት ረጅም ሰዓት መቀመጥ ብቻ አይደለም።
መማር ማለት፦
መረዳት ➡️ መለማመድ➡️ መተግበር ➡️ስህተትን ማረም ➡️ እንደገና መሞከር ነው። 🔄
👩🚀
እዚህ ላይ Magster ይመጣልMagster የተማሪዎችን የመማር ሂደት በቀላሉ እንዲከተሉ የተዘጋጀ የመማሪያ መድረክ ነው። 🎓
ትምህርቱን ብቻ ከመመልከት ይልቅ፣ ርዕሱን መረዳት፣ ምሳሌዎችን መከታተል እና በጥያቄዎች ላይ መለማመድ እንድትችል የሚረዳህን ይዘት ለማቅረብ እንሰራለን።
✈️
@magsteracademy